Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፓርቲዎች የሀሳብ ልዩነቶችን በማክበር ብሔራዊ ማንነት ላይ ያተኮረ እንቅስቃሴ ማድረግ ይገባቸዋል – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፖለቲካ ፓርቲዎች የትብብር ባህልን በማሳደግና የሀሳብ ልዩነቶችን በማክበር ብሔራዊ ማንነት ላይ ያተኮረ እንቅስቃሴ ማድረግ ይገባቸዋል አሉ ምሁራን።

ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ቆይታ ያደረጉት የየኒቨርሲቲ ምሁራን የፖለቲካ ፓርቲዎች የአርበኝነት ስሜትን በማዳበርና በኢትዮጵያ የተፈጠረውን የመድብለ ፓርቲ ልምምድ በአግባቡ በማስተዳደር ለሀገር እድገትና ዘላቂ ሰላም መስራት አንደሚገባቸው ጠቁመዋል።

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ እንዳለ ሙላቱ ለጠንካራ ሀገር ግንባታ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ መቆም እንዳለባቸው ተናግረዋል።

የተጀመረው የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ሥር እንዲሰድና ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥል ቅንጅታዊ ሥራዎች መሰራት አለባቸውም ነው ያሉት።

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ታምራት ዴላ በበኩላቸው÷ ፖለቲካ ፓርቲዎች የህግ የበላይነትና ህገመንግስታዊ ሥርዓትን አክብረው ሀገራዊ አንድነትና አካታችነት ማስፋፋት ላይ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

ገንቢ የሆኑ ፖሊሲዎችና ንድፈ ሀሳቦችን በማቅረብ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳች ቅድሚያ መስጠት እንደሚያስፈልግ ገልጸው÷ ብሔራዊ ማንነት ላይ ያተኮረ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባቸውም አመላክተዋል።

በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር የሆኑት ደረጄ ጥላሁን ፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ላይ የጀመሩትን አዎንታዊ ሚና እንዲያጠናክሩ ጠቅሰው÷ ተናበውና ተቀራርበው መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በፖለቲካ ፓርቲዎች ደረጃ ወሳኝ በሆኑ ሀገራዊ እሴቶች ላይ ስምምነት እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት ምሁራን÷ ተጠያቂነትና መልካም አስተዳደርን ሊያመጣ የሚችል ገለልተኛ ዴሞክራሲያዊ ተቋማት መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።

የሀሳብ ልዩነቶችን በማክበርና ዴሞክራሲን በማጎልበት ኢትዮጵያን ታላቅ ሀገር እንድትሆን የሚመጥናትን እንቅስቃሴ ሊያደርጉ እንደሚገባም መክረዋል።

በአስጨናቂ ጉዱ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version