Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጤና ሚኒስቴር ለኦቶና ሆስፒታል ከ55 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጤና ሚኒስቴር በቅርቡ በእሳት አደጋ ከፍተኛ ውድምት ለደረሰበት ኦቶና ሆስፒታል ከ38 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ለሆስፒታሉ አመራሮች በዛሬው ዕለት አስረክበዋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አባይነህ አበራ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ሆስፒታሉን በአጭር ጊዜ ውስጥ የተሻለ የሕክምና አገልግሎት ለሕብረተሰቡ እንዲሰጥ እየተሰራ ነው፡፡
ለዚህም የተለያዩ አካላት የሕክምና አገልግሎት ግብዓቶችን እና ሌሎች ድጋፎችን እያደረጉ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡
Exit mobile version