Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በክልሉ ለኢንቨስትመንት የተረከቡትን መሬት ባላለሙ 151 ባለሃብቶች ላይ ርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ18 ነጥብ 59 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 260 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡
የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አባስ መሐመድ (ዶ/ር)÷ ፈቃድ የተሰጠባቸው ዘርፎች ግብርና፣ አገልግሎት፣ ኢንዱስትሪ እና ሌሎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ፕሮጀክቶቹ ወደ ሥራ ሲገቡ ለ29 ሺህ 251 ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ነው የተናገሩት፡፡
የኢንቨስትመንት ፈቃድ ያወጡ ፕሮጀክቶች ያስመዘገቡት ካፒታል ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ5 ነጥብ 15 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው አንስተዋል፡፡
ከ15 ነጥብ 136 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 95 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደ ክልሉ ገብተው ለማልማት የጠየቁት መሬት ተላልፎላቸው ወደ ተግባር እንዲገቡ መወሰኑን አመልክተዋል፡፡
በክልሉ በሚገኙ ሁሉም አካባቢዎች ለሚገነቡ የኢንዱስትሪ ዞኖች የሚሆን ከ4 ሺህ 97 ሔክታር በላይ መሬት ዝግጁ መደረጉን ጠቁመዋል።
በበጀት ዓመቱ ለኢንቨስትመንት ልማት የተረከቡትን መሬት በአግባቡ ባላለሙ 151 ባለሃብቶች ላይ የተለያየ ደረጃ ያለው ርምጃ እንደተወሰደ ማብራራታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Exit mobile version