Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ታንዛኒያ ወደብ አልባ ሀገራትን የባሕር በር ተጠቃሚ ለማድረግ ቁርጠኛ ነኝ አለች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4 ፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ታንዛኒያ ወደብ አልባ የሆኑ ጎረቤት ሀገራትን የዳሬ ሰላም ወደብ ተጠቃሚ ለማድረግ ቁርጠኛ ነኝ አለች፡፡
ታንዛኒያ በ3ኛው የተባበሩት መንግስታት የባሕር በር የሌላቸው በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ጉባዔ ላይ÷ የባሕር በር የሌላቸው የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የዳሬ ሰላም ወደብን እንዲጠቀሙ ፍላጎት እንዳላት ገልጻለች፡፡
ሀገራቱ ለቀጣናው ሁነኛ የንግድ መስመር በሆነው ዳሬ ሰላም ወደብ ተጠቃሚ እንዲሆኑም በርካታ ተጨባጭ ሥራዎች መከናወን ጀምረዋል ነው ያለችው፡፡
ለአብነትም የወደቡን አቅም ማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ግንባታ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ አመልክታለች፡፡
የሀገራቱ የባሕር በር ተጠቃሚነት ከሚያስገኘው ዘርፍ ብዙ ጠቀሜታ ባሻገር የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን ሁለንተናዊ ትስስር ይበልጥ እንደሚያጠናክር ታምኖበታል፡፡
ታንዛኒያ መሰል ፍላጎት ያሳየችው በቀጣናው ያሉ ወደብ አልባ ሀገራት የባሕር ተጠቃሚ ለመሆን ከፍተኛ ፍላጎት ባሳዩበት ወቅት ነው፡፡
ኢትዮጵያና ኡጋንዳ የባሕር በር በማግኘት ኢኮኖሚያቸውን ለማሳደግ የሚያደርጉት ጥረት የሚበረታታ እንደሆነም አስገንዝባለች፡፡
ዓለም አቀፍ የባሕር በር ተጠቃሚነት መርሆች ወደብ አልባ ሀገራት የባሕር በር ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚደግፉ ቢሆኑም ጉዳዩ በተለያዩ ምክንያቶች ተፈጻሚ ባለመሆኑ በሀገራቱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
በአቤል ንዋይ

 

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Exit mobile version