Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኮሙዩኒቲ ሺልድ ፍፃሜ ጨዋታ…

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን የሆነው ሊቨርፑል በኮሙዩኒቲ ሺልድ የፍፃሜ ጨዋታ ከኤፍኤ ዋንጫ አሸናፊ ክሪስታል ፓላስ ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል።

በአርነ ስሎት የሚመሩት ሊቨርፑሎች በዌምብሌይ ስታዲየም ከክሪስታል ፓላስ ጋር የኮሙዩኒቲ ሺልድ ዋንጫን ለማንሳት አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ ይፋለማሉ።

ማንቼስተር ሲቲን በማሸነፍ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የኤፍኤ ዋንጫን ማንሳት የቻሉት ክሪስታል ፓላሶች ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሳተፉበት የኮሙዩኒቲ ሺልድ ዋንጫ ታሪክ ለመስራት ወደ ሜዳ ይገባሉ።

ከዚህ በፊት የኮሙዩኒቲ ሺልድ ዋንጫን ለ16 ጊዜ ማንሳት የቻለው ሊቨርፑል ለ17ኛ ጊዜ ዋንጫውን ለማሳካት ከክሪስታል ፓላስ ጋር የሚያደርገው ፉክክር ጨዋታው አጓጊ አድርጓል።

ከጨዋታው መጀመር በፊት በሞት ለተለየው የሊቨርፑል አጥቂ ዲዮጎ ጆታ የመታሰቢያ ሥነ ሥርዓት ይካሄዳል።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Exit mobile version