አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ከ100 ዓመት በኋላ ወደ ዓለም ዓቀፉ የስቶክ ገበያ ተመልሳለች አለ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ።
ተቋሙ በኢትዮጵያ ውስጥ ወርቅ በማምረት ከተሰማራው “አኮቦ ማዕድናት ኩባንያ” የ7 ነጥብ 4 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ በመግዛት የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ግብይት መፈጸሙን ገልጿል።
የመንግስት ልማት ድርጅቶችን የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የፈጸመው ግብይት ተቋሙ ከሀገር ውስጥ ገበያዎች ተሻግሮ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቱን ለማሳደግ መነሻ መሆኑን ጠቁሟል።
የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) በዓለም ዓቀፍ ኢንቨስትመንት ላይ መሰማራት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባለፈ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ በር የሚከፍት መሆኑን ተናግረዋል።
የአኮቦ ማዕድናት ኩባንያ ወርሃዊ የወርቅ ምርቱ ከ5 እስከ 10 ኪሎ ግራም መሆኑን አንስተው÷ ድርጅቱ የባለቤትነት ድርሻ መግዛቱን ተከትሎ የማምረት አቅሙ ከ50 እስከ 80 ኪሎ ግራም ከፍ እንደሚል ይጠበቃል ብለዋል።
ይህም ኢትዮጵያ ከ100 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዓለም አቀፉ ስቶክ ገበያ መመለሷን ያወጀችበት ታሪካዊ አጋጣሚ እንደሆነም አብራርተዋል።
በሞሊቶ ኤሊያስ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!