አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሔኖክ አርጋው ፋውንዴሽን ከ50 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ የሕክምና መሳሪያዎችና ግብዓቶችን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዳሉት ÷ ከዳያስፖራ እስከ ሀገር ቤት ያላቸውን ሃብት የሚያካፍሉ ቸር ልብ ያላቸው እልፍ ዜጎች አሉ።
ባዛሬው ዕለትም በአሜሪካ የሚገኘው ሔኖክ አርጋው ፋውንዴሽን ከ50 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ 133 አይነት የሕክምና መሳሪያዎችና ግብዓቶችን አበርክቶልናል ብለዋል።
መሳሪያዎቹ ለኩላሊት፣ ለተኝቶ ታካሚዎች፣ ለጽኑ እና መደበኛ ሕሙማን ሕክምና አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችሉ ተናግረዋል፡፡
ከንቲባዋ ፋውንዴሽኑ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውንም የከተማዋ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!