አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀረር ከተማ በ96 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ሪጅናል ላቦራቶሪ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በዚህ ወቅት÷ በክልሉ ለጤናው ዘርፍ ተደራሽነትና ጥራትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው ሪጅናል ላቦራቶሪም የጤና አገልግሎት ደረጃን የሚያሳድግና ከክልሉ ባለፈ የአጎራባች አካባቢ ማህበረሰብን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን አንስተው÷ ላቦራቶሪው በሙሉ አቅም አገልግሎት እንዲሰጥ ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ በሀገሪቱ ባለፉት ሰባት ዓመታት 28 የላቦራቶሪዎች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ጠቁመው÷ ውስብስብ ምርመራዎችን በማድረግ የጤናውን ዘርፍ አቅም ለማጎልበት ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው አብራርተዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አብዲ አሚን ሪጅናል ላቦራቶሪው ከዚህ ቀደም አገልግሎቱን በሚፈልጉ ዜጎች ላይ ሲደርስ የቆየውን እንግልትና ወጪን እንደሚያስቀር ተናግረዋል።
ጤና ሚኒስቴር እና ከሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የተገነባው ሪጅናል ላቦራቶሪው÷ የምርመራ አቅምን በማሳደግ የክልሉን የጤና ዘርፍ ለማጎልበት እንደሚያግዝም ተገልጿል።
በተስፋዬ ኃይሉ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!