Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ከአንጀሊና ጆሊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ከእውቋ አሜሪካዊት ተዋናይት እና የፊልም ባለሙያ አንጀሊና ጆሊ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ወደ ዓለም አቀፍ የጥበብ ኢንዱስትሪ መሳብ በሚችሉባቸው ዘዴዎች ላይ መክረዋል።
የኢትዮጵያን ታሪኮች በኢትዮጵያውያን መንገር ስላለው ጠቀሜታና ይህ በመላው አፍሪካም ሊሰራበት የሚገባ መሆኑንም መምከራቸውን አንስተዋል።
አንጀሊና ጆሊ በአዲስ አበባ ቆይታዋ የከተማዋ አንዱ አስደናቂ የቱሪስት መዳረሻ የሆነውን የብሔራዊ ቤተመንግስት ሙዚየምን ጎብኝታለች።
አንጀሊና ጆሊ ለኢትዮጵያ ላላት ልባዊ ፍቅር እና ቱሪዝምን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ለምታደርገው በጎ ድጋፍ የቱሪዝም ሚኒስትሯ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Exit mobile version