አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሰራቻቸው ስራዎች ተጨባጭ ለውጦች የተመዘገቡባቸው ናቸው አለ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴዔታ ስዩም መኮንን የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚሰራው ስራ ኢትዮጵያ ሚናዋን በአግባቡ እየተወጣች መሆኗን አንስተዋል።
እየተሰሩ ያሉ ስራዎችም ተጨባጭ ለውጥ የታየባቸው በመሆኑ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ የስበትና ተሞክሮ ማዕከል እየሆነች መምጣቷን ነው የገለጹት።
ኢትዮጵያ በመጭዎቹ ሳምንታት ዓለም አቀፍ ጉባዔዎችን እንደምታዘጋጅ አንስተው÷ ሁለተኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል።
በጉባዔው የኢትዮጵያ ተሞክሮ ለዓለም የሚገለጥበት እና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ውሳኔ የሚተላለፍበት እንደሆነም አመልክተዋል።
ለጉባዔው ስኬታማነት የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በሰለሞን ይታየው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!