አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጤና ሚኒስቴር ከ4 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የህክምና መሳሪያዎችን ለሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ አድርጓል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ በዚህ ወቅት÷ መንግስት የተሻለ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ እያከናወነ ባለው ተግባር አበረታች ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።
ለዜጎች ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎትን ለማስፋት የህክምና መሳሪያዎችን ማሟላት ትኩረት እንደተሰጠው አንስተው÷ የህክምና ተቋማትን ማስፋፋት፣ የህክምና መሳሪያዎችንና የመድኃኒት አቅርቦትን ማሟላት በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
እንዲሁም የዘርፉን ባለሙያዎች አቅም መገንባት ላይ በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑም አመልክተዋል።
ድጋፉ በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በኩል መደረጉን የገለጹት ሚኒስትሯ÷ ይህም የጤና አገልግሎትን ለማዘመንና ተደራሽ ለማድረግ ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር ነው ያስረዱት።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!