Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ በ 8 ሀገራት የችግኝ ተከላ ያከናውናሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ በሁለተኛው የወጣቶች ዓለም አቀፍ ችግኝ ተከላ (plant fraternity) መርሐ ግብር ፓኪስታንን ጨምሮ በስምንት ሀገራት ችግኝ ይተክላሉ።
የፓርቲው ወጣቶች ክንፍ ፕሬዚዳንት አክሊሉ ታደሰ 2ኛው የአረንጓዴ ዐሻራ ኢትዮጵያ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ያላትን ጸኑ አቋም የምታጋራበት ነው ብለዋል።
መርሐ ግብሩ በሀገራቱ ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን በትውልድ መካከል ትስስር የሚፈጥር እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን የሚጠናክር መሆኑን አመላክተዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩን የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ልምድ ለማካፈል ያለመ መርሐ ግብር መሆኑን አንስተው÷ የልዑክ ቡድኑ ሀገር በቀል ችግኞችን በመያዝ ወደ ፓኪስታን እንደሚያቀና ተናግረዋል።
በኢትዮጵያና በስምንቱ ሀገራት በሚገኙ የመጪው ትውልድ መካከል ህዝባዊ መሠረት ማጽናት የሚያስችል መርሐ ግብር መሆኑንም አብራርተዋል።
በመርሐግብሩ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ ሙና አህመድ እና በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር አቲፍ ሸሪፍ ሚያን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በሰማኸኝ ንጋቱ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Exit mobile version