Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ወጣቶች የሀገራቸውን የወደፊት ዕጣ ፋንታ የማሳመር ሂደት ላይ ሊሳተፉ ይገባል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ወጣቶች ሀገሪቱ ያለፈችባቸውን መንገዶች የማስተካከል ብቻ ሳይሆን መጪውን እጣ ፋንታዋን የማሳመር ሂደት ላይ ንቁ ተሳታፊ ሊሆኑ ይገባል አለ።

ምክክር ኮሚሽኑ ‘የወጣቶች ሚና ለውጤታማ ሀገራዊ ምክክር’ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከአማራ ክልል ወጣቶች ጋር የሚያካሂደውን ውይይት የመጀመሪያው ምዕራፍ ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ ጀምሯል።

በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር ብሌን ገብረ መድኅን እንዳሉት፤ ወጣቶች ኢትዮጵያ ያለፈችባቸውን መንገዶች የማስተካከል እና መጪውን እጣ ፋንታዋን የማሳመር ሂደት ላይ በንቃት መሳተፍ አለባቸው።

ከአሁን በፊት በነበሩ የምክክር ኮሚሽኑ ሂደቶች ወጣቶችን እንደ አንድ የማኅበረሰብ ክፍል መሳተፋቸውን አስታውሰዋል።

ይህንን ተሳትፎ ለማጠናከርም የተለያዩ የሃሳብ ግብአቶችን ለማግኘት ከተለያዩ ሙያዎች የተውጣጡ ወጣቶችን ማሳተፍ ማስፈለጉንም ተናግረዋል።

ከአማራ ክልል ወጣቶች ጋር የሚያካሂደው የመጀመሪያ ምዕራፍ ውይይት ለአራት ቀናት ይቆያል።

በመድረኩም በሀገራዊ ምክክር ሂደት የወጣቶች ተሳትፎና ሚና፣ በምክክሩ ሂደት የወጣቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎና አካታችነት እንዲጎለብት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሚና ተግባራት እና ሌሎች ሃሳቦች ላይ ውይይት ይደረጋል።

በደሳለኝ ቢራራ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Exit mobile version