Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለፖለቲካ ቀውስ ፍቱን መድኃኒት የሆነው የወል ትርክት …

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ ብሔራዊ ወንድማማችነትን ባከበረ መልኩ የወል ትርክትን መፍጠር ለሚያጋጥም የፖለቲካ ቀውስ ፍቱን መድኃኒት ነው አሉ።

“የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስብራቶች ከትናንት እስከ ዛሬ” በሚል መሪ ሀሳብ 44ኛ ጉሚ በለል እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ኃይሉ አዱኛ፤ ኢትዮጵያ በጠንካራ ዜጎቿ መስዋዕትነት ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ የቆየች ሀገር ናት ብለዋል።

የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች በሆነችው ሀገር ለዓመታት ሲተረክ የቆየው የነጠላ ትርክት የፖለቲካ ቀውስ ማስከተሉን አስታውሰዋል።

ከዚህ በተጨማሪም እየተስፋፋ የመጣውን ማህበራዊ ሚዲያ እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን በአሉታዊ መንገድ መጠቀም ቀውሱን ይበልጥ እንዳባባሰውም አንስተዋል።

በፖለቲከኞች ዘንድ የሀሳብ ልዩነቶችን በምክክርና በንግግር የመፍታት ጠንካራ ባህል አለመኖሩ ለቀውሱ መባባስ ሌላ ምክንያት እንደሆነም ተናግረዋል።

ይሁንና ብሔራዊ ወንድማማችነትን ባከበረ መልኩ የወል ትርክትን መፍጠር በሀገሪቱ ለተፈጠረው የፖለቲካ ቀውስ ፍቱን መድኃኒት ነው ብለዋል።

በውይይቱ ተሳታፊ የሆኑት የኦሮሚያ ክልል ግብርና ግብዓት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ብርሃኑ ሌንጂሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ዓመታትን ለዘለቀው የፖለቲካ አለመግባባት ሀገራዊ ምክክሩ ወሳኝ መፍትሄ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ይህም ለዘላቂ መግባባት ቀዳሚው አማራጭ መሆኑን ገልጸው፤ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ባህላችንን ለማሻሻልም ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መሰራት አለበት ብለዋል።

በታምራት ደለሊ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Exit mobile version