Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከዩ ኤን ቱሪዝም ጋር ሊሰራባቸው በሚችሉ የትብብር መስኮች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ከተባበሩት መንግስታት የቱሪዝም ተቋም ዋና ፀሐፊ ሼይካ አል ኑዌስ ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ውይይቱ የኢትዮጵያን ቀዳሚ የቱሪዝም የትኩረት አቅጣጫዎችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ከተቋሙ ጋር ሊሰራባቸው በሚችሉ የትብብር መስኮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ሚኒስትሯ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።

በዚህም የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች እና ኮንፈረንስ ቱሪዝምን ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በበይነ መረብ ከዋና ጸሐፊ ጋር መነጋገራቸውን ጠቁመዋል።

እንዲሁም በቅርቡ ይፋ የተደረገውን “Visit Ethiopia” መተግበሪያን ጨምሮ የዲጂታል አማራጮችን በተሻለ መልኩ መጠቀም በሚሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት መደረጉን አንስተዋል።

ነባር የባህል ቅርሶችን ለላቀ የቱሪዝም ተጠቃሚነት ማዋል በሚቻልበት እና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመቀናጀት ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ፍሰትን ማሳድግ የሚቻልበትን እምቅ አቅም በተመለከተም በውይይቱ መዳሰሱን አመልክተዋል።

Exit mobile version