Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዑለማዎች ምርጫ ሀይማኖታዊ አስተምህሮቱን ጠብቆ ተከናውኗል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አብዱልአዚዝ ኢብራሒም (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የተካሄደው የዑለማዎች ምርጫ ሀይማኖታዊ አስተምህሮቱን ጠብቆ ተከናውኗል አሉ፡፡

ሰብሳቢው ለፋና ዲጂታል እንደገለጹት÷ ምርጫው የበረከት ቀን በሆነው ጁምዓ በሁሉም ክልሎች ሁሉንም ባሳተፈ መልኩ ተካሂዷል።

እንደ አካባቢው የአር ሁኔታ ከሰዓት ጀምሮ የተከናወነው የዑለማዎቹ ምርጫ የሀይማኖት መሪዎች ተገኝተው ሀይማኖታዊ ስርዓት በማከናወን መጀመሩን አንስተዋል፡፡

በሁሉም ክልሎች የተደረገው ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ እና ግልፀኝነት የተሞለባት እንደነበር ገልፀው፤ በምርጫው ሙስሊሙ ማሕበረሰብ ለቀጣይ 5 ዓመታት ይወክለኛል የሚለውን ወኪል ካርድ ባወጣባቸው መስጅዶች ተገኝቶ ድምጽ ሰጥቷል ብለዋል፡፡

ከነገ ጀምሮ ደግሞ የምሁራን፣ የወጣቶች፣ የሴቶችና የሠራተኛውን ማሕበረሰብ ለሚወክሉ ተመራጮች ድምጽ ይሰጣል ብለዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

Exit mobile version