Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሚድሮክ ሳምንት አውደ ርዕይ ከነሐሴ 26 ጀምሮ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ “ሚድሮክ ለሀገር” በሚል መሪ ሐሳብ ከነሐሴ 26 ጀምሮ ለአምስት ቀናት የሚቆይ አውደ ርዕይ ያካሂዳል።
አውደ ርዕዩ ሚድሮክ ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን ትስስር ለማጠናከር ያለመ መሆኑን የግሩፑ ኮሙኒኬሽንና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር አቶ ሁናቸው ታዬ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
ግሩፑ ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን ትስስር ለማጠናከርና ቀጣይ የትኩረት መስኮችን ለማሳወቅ ያለመ አውደ ርዕይ መሆኑንም አንስተዋል።
በአውደ ርዕዩ የሚድሮክ ግሩፕ ድርጅቶች ምርትና አገልግሎታቸውን ይዘው በመቅረብ የገበያ ትስስር እንደሚፈጥሩም አመልክተዋል።
ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የሚሳተፉበት የፓናል ውይይት እንደሚደረግም ተገልጿል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version