አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ተንታ ወረዳ በተከሰተ የመሬት ናዳ የአንድ አርሶ አደር ቤተሰብ አባላት የሆኑ የአራት ሰዎች ሕይወት አልፏል።
የተንታ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ ወርቅነህ መላኩ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ አደጋው ቋጥኝ ድንጋይ ተንዶ መኖሪያ ቤት ላይ በመውደቁ ነው የተከሰተው፡፡
በዚህም በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የነበሩ አራት የአንድ አርሶ አደር ቤተሰብ አባላት ሕይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል፡፡
እስካሁን የአንድ ሰው አስከሬን መገኘቱን ጠቁመው÷ የሌሎቹን ሦስት ሰዎች አስከሬን ለማውጣት ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
የተጫናቸው ቋጥኝ ድንጋይ ከባድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የአስከሬን ማውጣት ሥራውን አስቸጋሪ እንዳደረገውም አመልክተዋል፡፡
በአቤል ነዋይ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡