አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደብረ ታቦር ዓመታዊ በዓል በዛሬው ዕለት በደብረታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ተከብሯል፡፡
በዓሉ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ ነሐሴ 13 የሚከበር ሲሆን÷ በደብረታቦር ከተማ ርዕሰ አድባራት ደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ሐይማኖታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡
በክብረ በዓሉ ላይ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ መልካሙ ፀጋዬ እና የደብረ ታቦር ከተማ ከንቲባ አቶ ደሴ መኮንንን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ከበዓሉ አከባበር ጎን ለጎን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በደብረታቦር ኢየሱስ ሙዚየም ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጡን የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ እምቢያለ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
በሚኪያስ አየለ