አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ዘንድሮ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተጀመረ ወዲህ ከ1 ሚሊየን በላይ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ተሳትፈዋል አለ።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አቢቲ ኢንሰቦ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፤ በወጣቶች የክረምቱ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ2 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት አገልግሎት ይሰጣል።
4 ሚሊየን የሚሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል።
በዚህም የአረንጓዴ አሻራ፣ የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ እና መገንባትን ጨምሮ ወደ 14 በሚሆኑ የስራ መስኮች ላይ ወጣቶች ተሰማርተው አገልግሎት እየሰጡ ነው ብለዋል።
የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተጀመረ ወዲህ ከ1 ሚሊየን በላይ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ተሳትፈዋል ነው ያሉት።
በወጣቶች በተከናወኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባለፉት 90 ቀናት ውስጥ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰው፤ አገልግሎቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
በክልሉ እየተከናወነ የሚገኘው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአንድ ጊዜ ተግባር ከመሆን አልፎ ወደ ባህልነት እየተቀየረ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ሁሉም ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ በትጋት እንዲሳተፉ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

