Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያን ስም በዓለም ከፍ ያደረገው የአረንጓዴ አሻራ…

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአረንጓዴ አሻራ የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል፣ በኢኮኖሚ እና ምርታማነትን በማሳደግ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ ያደረገ ተግባር ነው አሉ ምሁራን።

በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም መሪ ሥራ አስፈጻሚ ፋኖሴ መኮንን እንዳሉት÷ የአረንጓዴ አሻራ የኢትዮጵያን የደን ሽፋን በመጨመር ረገድ ተጨባጭ ውጤት አስመዝግቧል፡፡

በዚህም የካርበን ልቀትን በመቀነስ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለጎረቤትና ለዓለም ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ከመዋጋት አንጻር አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡

መንግስት ለጉዳዩ ያሳየው ቁርጠኝነትና በመርሐ ግብሩ የተገኘው ውጤት ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ያላት ተጽዕኖ እንዲጨምር እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

በሌሎች ሀገራት መገናኛ ብዙሃን በስፋት ሽፋን እያገኘ እና ልምድ በመውሰድ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።

የዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪው ጌትዬ ትርፌ (ዶ/ር) በበኩላቸው የአየር ንብረት ለውጥ አሁን ላይ የዓለም ፈተና መሆኑን ጠቁመው÷ በርካታ አሉታዊ ጫናዎች እያሳደረ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

ይህንን ፈተና ለመጋፈጥ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ያስመዘገበችው ውጤት ብሎም ለአየር ንብረት ለውጥ የሰጠችው ትኩረት የሚበረታታ ተግባር በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ውጤት ለአፍሪካ ብሎም ለዓለም በስፋት ማስተዋወቅ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

መርሐ ግብሩን በቀጣይ አጠናክሮ ለማስቀጠል ሁሉም ዜጋ በንቃት መሳተፍ እንደሚጠበቅበትም ምሁራኑ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version