አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት አምስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ፡፡
በዚህ መሰረትም ቀን 8 ሰዓት ከ30 ላይ ማንቼስተር ሲቲ ከቶተንሃም ሆትስፐር የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡
በመጀመሪያው ሳምንት ጨዋታ ሲቲ ዎልቭስን 4 ለ ዐ እንዲሁም ቶተንሃም አዲስ አዳጊውን በርንሌይ 3 ለ ዐ ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች ድላቸውን አጠናክረው ለማስቀጠል በዛሬው ዕለት ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል በርንማውዝ ከወልቭስ፣ በርንሌይ ከሰንደርላንድ እና ብሬንትፎርድ ከአስቶንቪላ በተመሳሳይ አመሻሽ 11 ሰዓት ይጫወታሉ፡፡
እንዲሁም ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ አርሰናል ሊድስ ዩናይትድን በኤምሬትስ ስታዲየም የሚያስተናግድ ይሆናል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast