Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአንጎለላና ጠራ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የ2 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላና ጠራ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።

አደጋው የደረሰው 19 ተሳፋሪዎችን ጭኖ ከደብረብርሀን ወደ አዲስ አበባ ከተማ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ ሀይሩፍ በሚል የሚታወቀው አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ነው።

የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ኮማንደር በልኬ ይርጋ እንዳሉት፤ ፍጥነት ላይ የነበረው ተሽከርካሪ ጨኪ ቀበሌ ልቼ ጎጥ አካባቢ ጎማ ፈንድቶበት ሊገለበጥ ችሏል።

በዚህም የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 10 ተሳፋሪዎች ከባድ የአካል ጉዳት እንዲሁም ሰባት ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት እንዳጋጠማቸው ገልጸዋል።

አሽከርካሪው ለጊዜው ከስፍራው መሰወሩን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የተናገሩት ኮማንደር በልኬ ይርጋ፤ የፍጥነት ወሰኑን አክብሮ በማሽከርክር በሰው እና በንብረት ላይ የሚደርሰውን ውድመት በጋራ እንከላከል ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በታለ ማሞ

Exit mobile version