አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ተለዋዋጭ በሆነው ዓለም ውስጥ የአፍሪካን ነገ ሊወስኑ የሚችሉ ሥራዎችን በትብብር ማከናወን ያስፈልጋል አሉ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፡፡
የአፍሪካ የትምህርት ምዘናዎች ኅብረት 41ኛ ዓመታዊ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የዓለም ስልጣኔ ለውጥ ላይ በመሆኑ የአፍሪካን ቀጣይ መዳረሻ ማሰብና መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
በተለያዩ ዘርፎች የኢትዮጵያንም ሆነ የአፍሪካን የነገ መዳረሻ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመገንባት በትብብር መስራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በቀጣይ አፍሪካን ያቀፈ ለውጥ ለማረጋገጥ የነገ መዳረሻን ሊወስኑ በሚችሉ የግብርና፣ ኃይል ልማት፣ መሰረተ ልማትና ትምህርት ዘርፍ ላይ መስራት ይገባል ነው ያሉት፡፡
የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ የትምህርት ምዘናን ከምዘና ባሻገር ለአጠቃላይ ትምህርት ስኬት ማዋል አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የትምህርት ምዘና ከፈተና የተሻገረ የትምህርት አጋዥ አቅም መሆኑን ጠቁመው÷ ሥራው ስኬታማ እንዲሆን ቀጣይነት ባለው መልኩ በቅንጅት መሥራትን ይጠይቃል ብለዋል።
በለይኩን ዓለም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!