Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ቡካዮ ሳካ ለአራት ሳምንታት ከሜዳ ይርቃል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እንግሊዛዊው የአርሰናል የመስመር አጥቂ ቡካዮ ሳካ በጉዳት ምክንያት ለአራት ሳምንታት ከሜዳ ይርቃል፡፡

ተጫዋቹ ባሳለፍነው ቅዳሜ ምሽት አርሰናል ሊድስ ዩናይትድን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ባሸነፈበት ጨዋታ ጉዳት አስተናግዶ ከሜዳ መውጣቱ ይታወሳል፡፡

ሳካ በጨዋታው ላይ የአርሰናልን 2ኛ ግብ ከመረብ ያገናኘ ሲሆን፥ ለአራት ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡

ይህን ተከትሎ አርሰናል በመጪው እሁድ በፕሪሚየር ሊጉ ከሊቨርፑል ጋር የሚያደርገው ተጠባቂ ጨዋታ እንደሚያመልጠው ዘገባው አመልክቷል፡፡

በተመሳሳይ ከሊድስ ጋር በነበረው ጨዋታ ጉዳት አስተናግዶ የነበረው ማርቲን ኦዲጋርድ ለአንፊልዱ ፍልሚያ የመድረሱ ጉዳይ አጠራጣሪ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

Exit mobile version