Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመንገድ መሰረተ ልማት የብልፅግና ጉዞን ለመደገፍ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ ይገኛል – ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ የመንገድ መሰረተ ልማት ሁሉን አቀፍ ልማት ለማፋጠንና የብልፅግና ጉዞን ለመደገፍ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ ነው አሉ።

ሀገር አቀፍ የመንገድ ዘርፍ ጉባኤ ‘በጋራ ኢትዮጵያን እንገንባ’ በሚል መሪ ሀሳብ በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በመድረኩ እንዳሉት፤ የመንገድ ግንባታ በመንግስት ከፍተኛ ትኩረት ከተሰጣቸው የመሠረተ ልማት ዘርፎች መካከል አንዱ ነው።

በየአካባቢው የምንተገብራቸው የመንገድ መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ከመንገድ ባሻገር ገበያ፣ የዕድል እና የስልጣኔ በር መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

በመሆኑም ሁሉም ባለድርሻዎች ለመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ተገቢውን ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ መሀመድ በበኩላቸው፤ ጉባኤው ለሀገራችን አይተኬ ሚና ባለው በመንገድ ልማት ላይ የሚካሄድ በመሆኑ ትልቅ ፋይዳ አለው ነው ያሉት፡፡

በሶማሌ ክልል መንገድን ጨምሮ እየተከናወኑ የሚገኙ የመሠረተ ልማት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

በቤዛዊት ከበደ

Exit mobile version