Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

2 ሺህ 900 ሜትር የሚረዝመው ድልድይ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቻይና እየተገነባ የሚገኘው ረጅሙ ድልድይ በቅርቡ ተጠናቆ ለአገልግሎት ይበቃል።

በደቡብ ምዕራብ ቻይና ጉጆ ግዛት የተገነባው ረጅሙ ድልድይ ወደ ስራ ከመግባቱ አስቀድሞ ፍተሻ እየተደረገለት ይገኛል።

ባለፉት አምስት ቀናት የመጫን አቅሙ የተፈተሸው ይህ ድልድይ የታለመለትን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል አስተማማኝ አቅም እንዳለው ተረጋግጧል ተብሏል፡፡

የድልድይ ግንባታው መሐንዲሶች እንዳሉት÷ የድልድዩን አቅም ለመፈተሽ 96 የጭነት ተሽከርካሪዎች በአንድ ጊዜ ተከታትለው እንዲያልፉበት ተደርጓል።

የድልድዩ ግንባታ የመንገድ ደህንነት መስፈርቶች ጨምሮ ደረጃውን ጠብቆ የተከናወነ ነው ብለዋል።

በዓለም ላይ ረጅሙ ድልድይ ለመባል በፍጻሜ ዋዜማ ላይ የሚገኘው ይህ ድልድይ ከመሬት በላይ ያለውን 1 ሺህ 420 ሜትር ጨምሮ አጠቃላይ ርዝመቱ 2 ሺህ 900 ሜትር ነው።

ይህም በአለም የመጀመሪያው ረጅሙ ድልድይ እንዲሆን ያስቻለው ሲሆን በተራራማ አካባቢ የተገነባ ብቸኛው የዓለማችን ድልድይ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ቻይና ዘመናዊ ድልድዮችን በመገንባት ከዓለም በመሪነት ደረጃ የተቀመጠች ሲሆን በ’ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ’ አፍሪካን ጨምሮ ዓለምን በመንገድ መሰረተ ልማት ለማስተሳሰር እየሰራች እንደምትገኝ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ

Exit mobile version