አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 15ኛው የምስራቅ አፍሪካ ኮሙኒኬሽን ማህበር ዓመታዊ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
ጉባዔው “ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ለአፍሪካ ትስስር” በሚል መሪ ሃሳብ ነው በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በመድረኩ የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር)፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሳሙዔል ክፍሌ (ዶ/ር) እና የምስራቅ አፍሪካ ኮሙኒኬሽን ማህበር ፕሬዚዳንት ማርጋሬት ጁኮ (ፕ/ር) ተገኝተዋል፡፡
በተጨማሪም ከአባል ሀገራቱ የተውጣጡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ ተመራማሪዎች እና አጋር አካላት ተሳትፈዋል፡፡
ለሶስት ቀናት የሚቆየውን ጉባዔ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በትብብር አዘጋጅቶታል፡፡
በመራኦል ከድር
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!