አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ/ ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል መከላከል ቡድን 50ኛ የከፍተኛ ሃላፊዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
በጉባዔው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምጸሐይ ጳውሎስ፣ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሙሉቀን አማረ እና የቡድኑ ሊቀ መንበር ፍሬዘር አያሌው ተገኝተዋል፡፡
የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል መከላከል ቡድን ዓመታዊ ጉባዔ ከነሐሴ 16 እስከ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
በዛሬው ዕለት የተጀመረው የቡድኑ ከፍተኛ ሃላፊዎች ጉባዔም የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል መከላከል ቡድን ዓመታዊ ጉባዔ አካል ነው፡፡
በጉባዔው ከአባል ሀገራቱ፣ ከአንድ ታዛቢ ሀገር እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የተወጣጡ 1 ሺህ 150 በላይ ተወካዮች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ በቀጣናው በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል መከላከል ላይ በንቃት እየተሳተፈች እንደምትገኝ በመድረኩ ተነስቷል፡፡
በዘርፉ የሕግ ማሻሻያ ከማድረግ ጀምሮ ከተለያዩ ሀገራት ጋር በትብብርና በቅንጅት እየሰራች መሆኑም ተጠቁሟል።
በዓለምሰገድ አሳዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!