Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሲዳማ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለማስጀመር ዝግጅት ተደርጓል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋና ዘመናዊ ለማድረግ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማስጀመር ዝግጅት ተደርጓል አሉ።
አቶ ደስታ ሌዳሞ እንዳሉት፤ የልማት፣ የአገልግሎት አሰጣጥና አጠቃላይ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተደረገው ጥረት ውጤት ተገኝቷል።
ከለውጡ በኋላ የሚታዩና የሚጨበጡ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸው፤ ለህዝቡ የልማትና የአገልግሎት ፍላጎቶች ምላሽ ለመስጠት የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደቀጠሉ ነው ብለዋል።
የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት፣ ፈጣንና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ ዘመናዊና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት መዘርጋት የግድ መሆኑን አንስተዋል።
ለዚህም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማስጀመር የሰው ሀይል፣ የሕንጻ እና መሰል ዝግጅቶች እየተደረጉ ይገኛል ነው ያሉት።
ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ሥራዎችን ለማሳካት እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ዝግጁነት ስለመኖሩ ማስረዳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Exit mobile version