Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠንካራ የቴክኖሎጂ ቁመና ለመገንባት …

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ጠንካራ የቴክኖሎጂ ቁመና ለመገንባት የሚያስችሉ ስራዎች ላይ ርብርብ ይደረጋል አሉ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የክልል ቢሮዎች የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም እና የ2018 በጀት ዓመት ስራዎች ዕቅድ ግምገማ በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ እንዳሉት፤ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት በርካታ ቁልፍ ተግባራትን በማከናወን የተሻለ አፈፃፀም ተመዝግቧል።

በበጀት ዓመቱ ለዜጎች የስራ ፈጠራ ጉልህ ሚና የሚያበረክተውን የስታርት አፕ አዋጅ እንዲፀድቅ ማድረግን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

የታዩ ክፍተቶችን በማረም እና የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል ተቋማዊና ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ቁመና ለመገንባት የሚያስችሉ ስራዎች ላይ ርብርብ ይደረጋል ነው ያሉት።

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ በበኩላቸው፤ በአስተዳደሩ ዲጂታል ድሬን እውን ለማድረግ ተስፋ ሰጪ ፈጠራዎች ጎልተው እንዲወጡ ተደርጓል ብለዋል።

የአገልግሎት አሰጣጥን ለማላቅና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በተስፋዬ ኃይሉ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version