Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሀረሪ ክልል ለ2018 በጀት ዓመት 8 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀረሪ ክልል ምክር ቤት የክልሉን የ2018 በጀት ከ8 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ በማድረግ አጽድቋል።
ምክር ቤቱ ባካሄደው 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 8ኛ መደበኛ ጉባኤ የክልሉን የ2018 በጀትን ከ 8 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ በማድረግ አጽድቋል።
የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ መሀመድ ያህያ ከተያዘው በጀት 5 ቢሊየን 640 ሚሊየን 802 ሺህ 726 ብር ለካፒታል በጀት የተመደበ መሆኑን ጠቁመዋል።
2 ቢሊየን 966 ሚሊየን 401 ሺህ 081ብር ለመደበኛ በጀት የሚውል ነው ብለዋል።
በጀቱም በዋናነት ከክልሉ ከሚሰበሰብ ገቢ እና ከፌዴራል መንግስት በሚገኝ ድጎማ የሚሸፈን መሆኑን ገልፀዋል።
የፀደቀው በጀት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ50 በመቶ ብልጫ እንዳለውም መጠቆማቸውን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ሔኖክ ሙሉነህ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Exit mobile version