Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኮሚሽኑ በሰሜን አሜሪካ አጀንዳ የማሰባሰብ መድረክ ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ነሐሴ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ የሚያሰባስብበት መድረክ ያካሂዳል፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መላኩ ወ/ማርያም እንደተናገሩት፤ ኮሚሽኑ የመንግስት ሳይሆን የህዝብ በመሆኑ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በዚህ በተዘረጋ ታሪካዊ ዕድል በንቃት መሳተፍ አለባቸው፡፡

በምክክር መድረኩ ለስደት የዳረጓቸውን የሀገራቸውን ስር የሰደዱ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ችግሮች በማንሳት አጀንዳ እንዲያቀርቡም ተጠይቋል፡፡

ይህንን ጉዳይ በአጀንዳ ቢያቀርቡ ሲመለሱ የምትመቻቸው ሀገር መፍጠር እንደሚችሉም ነው የተገለፀው፡፡

በአካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ብዥታ ከሚፈጥሩ ነገሮች ራሳቸውን እንዲያርቁ እና በምክክሩ ላይ መሳተፍ እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡

ሁሉም በምክክር መድረኩ በመሳተፍ ሀገራዊ ፋይዳቸው የጎላ አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ እንዲያስረክቡ ጥሪ መቅረቡን ኮሚሽኑ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version