Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቀድሞ ታጣቂዎች በስልጠና ባገኙት የጠራ ግንዛቤ ሕዝባቸውን በቅንነት ሊያገለግሉ ይገባል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀድሞ ታጣቂዎች ከተሃድሶ ስልጠናው ባገኙት የጠራ ግንዛቤ ሕዝባቸውን በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል ይጠበቅባቸዋል አለ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን።
በጠዳ የተሃድሶ ስልጠና ማዕከል ለአንድ ሳምንት የተሰጣቸውን ስልጠና ያጠናቀቁ የቀድሞ ታጣቂዎች የሽኝት ሥነ ሥርዓት ዛሬ ተካሂዷል።
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ተወካይ አቶ ግዛቸው መኩሪያ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ፥ የቀድሞ ታጣቂዎች ሰላም ፈላጊ መሆናቸውን በስልጠናው ሒደት ማረጋገጥ ተችሏል።
ከስልጠናው በኋላ ወደ ሕብረተሰቡ በመቀላቀል በሚጀምሩት አዲስ ሕይወት የሠላም አምባሳደር በመሆን ሕዝቡን በታማኝነት ሊያገለግሉ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
ኮሚሽኑ የቀድሞ ታጣቂዎች በአጭር ጊዜ ተቋቁመው ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ የጀመራቸውን የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች በትኩረት እያከናወነ መሆኑን አንስተዋል።
በአማራ ክልል የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ የቀድሞ ታጣቂዎች በተሃድሶ ስልጠናው አልፈው ሕዝቡን በልማት መካስ እንዲችሉ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
የሄዱበት መንገድ የተሳሳተ መሆኑን ተገንዝበው የተመለሱ የቀድሞ ታጣቂዎች የሠላም ጥሪውን ከልብ ተቀብለው መግባታቸው አዎንታዊ ርምጃ ነው ያሉት ደግሞ የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ም/ሃላፊ አቶ በሪሁን መንግስቱ ናቸው።
የክልሉ መንግስት የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ሕብረተሰቡ ተቀላቅለው በዘላቂነት የሚቋቋሙበትን አሰራር ዘርግቶ ተግባራዊ እያደረገ ነው ማለታቸውንም ኢዘኤ ዘግቧል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Exit mobile version