Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአካባቢው የሰፈነው ሰላም የነቀምቴ ከተማን ልማት ለማፋጠን ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአካባቢው የሰፈነው ሰላም በነቀምቴ ከተማ ሰፊ የልማት ተግባራትን ለማፋጠን ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል አሉ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ሰአዳ አብዱራህማን፡፡
አፈ ጉባዔዋ በነቀምቴ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በዚህም ባሕላዊ ፍርድ ቤቶችን፣ የኢኒሼቲቨ ሥራዎችን፣ የኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታና የሚስማር ፋብሪካን የሥራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡
አፈ ጉባዔ ሰአዳ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ በአካባቢው የሰፈነው ሰላም በነቀምቴ ከተማ ሰፊ የልማት ተግባራትን ለማፋጠን ምቹ መደላድል ፈጥሯል።
በፌዴራል እና ክልል መንግስት በተሰጠው ትኩረት ከተማዋ በፈጣን የእድገት ጎዳና ላይ እንደምትገኝ ጠቁመው÷ ይህም የተያዘውን የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት ያግዛል ነው ያሉት፡፡
ሕብረተሰቡ በሰላም ግንባታና የልማት ሥራዎች ላይ ተሳትፎውን ይበልጥ በማጠናከር የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ማስገንዘባቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Exit mobile version