Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሴንት ኪትስ እና ኔቪስ ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሴንት ኪትስ እና ኔቪስ ጠቅላይ ሚኒስትር  ቴራንስ ድሬው (ዶ/ር) በሁለተኛው የአፍሪካ ካሪቢያን ማህበረሰብ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የማዕድን ሚኒስትሩ ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሁለተኛው የአፍሪካ ካሪቢያን ማህበረሰብ ጉባዔ “ለአፍሪካውያንና ዘርዓ አፍሪካውያን የማካካሻ ፍትህን ለመሻት አህጉር ተሻጋሪ አጋርነት” በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ጉባዔው የአፍሪካና ካሪቢያን ሀገራት በደቡብ ደቡብ የትብብር መንፈስ ግንኙነታቸውን ለማጎልበት፣ አፍሪካ ከካረቢያን ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ወደ ጠንካራ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ እና ትብብር ለማሳደግ ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ጉባዔው በዓለም የፋይናንስ ስርዓት፣ በቱሪዝም፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ይመክራል።

በአሸናፊ ሽብሩ

Exit mobile version