Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

 የኢትዮጵያውያንን የመኖሪያ ቤት ችግር መፍታት የምኖርለት ዓላማ ነው – አቶ ዮናስ ታደሰ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦቪድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዮናስ ታደሰ የኢትዮጵያውያንን የመኖሪያ ቤት ችግር መፍታት የምኖርለት ዓላማ ነው አሉ፡፡

ዋና ስራ አስፈፃማው ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ ኦቪድ ግሩፕ የቤት ቸግርን ለመፍታት በውስን ቦታዎች ላይ በርካታ የመኖሪያ መንደሮችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋለ፡፡

ድርጅታቸው በዋናነት ውስን ቦታዎች ላይ እንደ ደንበኞች ፍላጎት ከአንድ ክፍል ጀምሮ እስከ አፓርትመንት ድረስ በመገንባት ለሽያጭ እያቀረበ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

ኦቪድ በአይነት እና በዲዛይን የተሻሻሉ ቤቶችን እገነባ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው÷ በዚህም ኢትዮጵያውያንን በተመጣጣኝ ዋጋ የቤት ባለቤት እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በተለይም ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ከ850 ሺህ ብር ጀምሮ መጠነኛ የመኖሪያ ቤት ክፍሎችን ለሽያጭ ለማቅረብ ዝግጅቶችን ማጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያውያንን የመኖሪያ ቤት ችግር መፍታት የምኖርለት ዓላማ ነው የሚሉት አቶ ዮናስ ታደሰ÷ ለዚህም ድርጅታቸው ኦቪድ ግሩፕ ያለእረፍት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

Exit mobile version