Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

 የጎቤ እና የሺኖዬ ጨዋታ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጎቤ እና የሺኖዬ ጨዋታ በኦሮሞ ባህልና እሴት መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የጎቤና እና ሺኖዬ ወደ በጋው ብርሃን ሽግግር እና ለፀደይ ንጋት አቀባበል በተለያዩ ቅርጾች የሚካሄድ ባህላዊ ጨዋታ ነው።

ጨዋታውን ባለትዳር ያልሆኑ ከ12 እስከ 25 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ብቻ የሚሳተፉበት ሲሆን÷ ቄሮና ቀሬዎች በዘፈን፣ በመብላት እና በመጠጣት እንዲሁም ስጦታ እየተሰጣቸው ያከብሩታል።

ትዳር ያላቸው ሽማግሌዎች እና ጎልማሶች ደግሞ ቄሮና ቀሬዎችን በየቤታቸው እየተቀበሉ ይመግቧቸዋል፤ ያጠጡዋቸው፤ ይባርኳቸዋልም።

Exit mobile version