Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ያጠናቀቅናቸው ታላላቅ ፕሮጀክቶች በኅብረት ከሰራን የሚያቅተን ነገር እንደሌለ ህያው ምስክሮች ናቸው – አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኅብረት ከሰራን የሚያቅተን ነገር አለመኖሩን ሰርተን ያጠናቀቅናቸው ታላላቅ ፕሮጀክቶቻችን ህያው ምስክሮች ናቸው አሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ።

ርዕሰ መስተዳድሩ “ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ የሚገኘውን የኅብር ቀን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት፥ በኅብር ውስጥ ባለን አንድነትና ኅብረት መቻላችንን አሳይተናል ብለዋል።

ኢትዮጵያ በብዝኃነት ውስጥ አንድነታቸውን የጠበቁ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ልዩ ማህበራዊና ባህላዊ እሴቶች የተገነቡባት ድንቅ የሕዝቦች ሙዚየም መሆኗን ጠቁመዋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዘመን በተሻገረ አብሮነት የተጋመዱ፥ ባህል እሴቶቻቸውን ተወራርሰው የተሰናሰሉ ኅብር ህዝቦች የሚኖሩበት የሕብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያ ነፀብራቅ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

የክልሉ ህዝቦች በብዝኃነት ውስጥ ያበበ አንድነታቸውን አፅንተው በጋራ ለሰነቁት የሰላምና የብልጽግና ትልም ስኬት በኅብረት በመትጋት በስኬት የታጀበ ጉዞ እያደረጉ ነው ብለዋል።

በማንሰራራት ላይ የምትገኘው ሀገራችን ሁለንተናዊ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ በስኬት ቀጥላለች ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ኢትዮጵያውያን ታላቁ የህዳሴ ግድብን በማጠናቀቅ በኅብረት መቻላቸውን ለዓለም ያሳዩበት እንደሆነ አመልክተዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version