Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፍሪካና ካሪቢያን ሀገራት በቅኝ ግዛት ወቅት ለተፈጸመባቸው በደል ፍትሕ ሊጠይቁ ይገባል – መሐመድ አሊ ዩሱፍ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ እና ካሪቢያን ሀገራት በቅኝ ግዛት ወቅት ለተፈፀሙ በደሎች በጋራ ፍትሕ መጠየቅ አለባቸው አሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ
2ኛው የአፍሪካ ካሪቢያን ሀገራት መሪዎች ጉባዔ “ለአፍሪካውያንና ዘርዓ አፍሪካውያን የማካካሻ ፍትሕን ለመሻት አህጉር ተሻጋሪ አጋርነት” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
መሐመድ አሊ ዩሱፍ በዚህ ወቅት በስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት÷በታሪክ ለተፈፀሙ በደሎች እውቅና እንዲሰጥ፣ ትርጉም ያለው ካሳ እንዲያገኙና ሁሉን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፍትሃዊ ሥርዓት እንዲኖር ሀገራቱ በጋራ መታገል አለባቸው።
ጉባዔው እነዚህና ሌሎች የጋራ የሆኑ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመሥራት መልካም አጋጣሚ እንደሚሆንም አንስተዋል።
አፍሪካውያን የማካካሻ ፍትሕ ለማግኘት የጀመሩት ጥረት ስኬታማ የሚሆነው ከካሪቢያን ሀገራት ወንድሞቻቸው ጋር በትብብር ሲሰሩ እንደሆነ ህብረቱ ያምናል ነው ያሉት፡፡
አፍሪካና ካሪቢያን ቀደምት አባቶች ያኖሩትን የታሪክ ትስስር መሠረት በማፅናት ለጋራ ነጻነትና ፍትሕ እንዲሁም ብልጽግና በቅንጅት መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አንስተዋል፡፡
ጉባዔው የአፍሪካና ካሪቢያን ሀገራትን ግንኙነት ለማጎልበት፣ ግንኙነቱን ወደ ጠንካራ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ እና ትብብር ለማሳደግ እንደሚያስችልም ተመላክቷል፡፡
በአንዷለም ተስፋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Exit mobile version