አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሟን ለማረጋገጥ ወደ ኋላ የሚጎትታት ነገር እንደሌለ ያሳየንበት ነው አሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ከበደ ዴሲሳ።
ሚኒስትር ዴዔታው እንዳሉት ÷ ዓባይን አልምቶ ለሀገር እድገት ማዋል አለመቻል የኢትዮጵያውያን የዘመናት ቁጭት ነበር፡፡
ይህን ቁጭት ለመቀየርም ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት በመቆም የሕዳሴ ግድብ ግንባታን በራስ ሃብትና አቅም ማጠናቀቅ ችለናል ብለዋል።
የሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ዜጎች ለአንድ ግብ ከተባበርን ብሄራዊ ጥቅማችንን ከማረጋገጥ ወደ ኋላ የሚጎትተን ነገር እንደሌለ ያረጋገጥንበት ነው ሲሉም አውስተዋል፡፡
መንግስት የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት እንደ ሕዳሴ ግድብ ያሉ በርካታ የልማት ሥራዎችን አቅዶ እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡
ዜጎች በቀጣይ የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም ለማረጋገጥ በሚሰሩ ተግባራት ላይ ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።
ኢትዮጵያ ብዝሃነት ጎልቶ የሚንጸባረቅባት፣ የበርካታ ተፈጥሮ ሃብት ባለቤት መሆኗን ገልጸው ÷ ይህን ወደ ልማት ለመቀየር ጠንካራ ሥራ መስራት ይገባል ነው ያሉት፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ምሳሌ የሆነ ሀገራዊ ፕሮጀክት እንደሆነም አውስተዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!