አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቅቆ መመረቅን አስመልክቶ በመስቀል አደባባይ ለሚካሄደው የድጋፍ ሰልፍ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ።
ለድጋፍ ሰልፉ የተወሰኑ መንገዶች ዝግ እንደሚደረጉ ያስታወቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ፤ በመዲናችን መስቀል አደባባይ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ የተዘጋጀ ሲሆን መርሀ ግብሩን ምክንያት በማድረግ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ ብሏል።
በዚህም መሠረት ከመስከረም 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ የድጋፍ ሰልፉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የሚከተሉት መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ማቆም እንዲሁም ዝግ ይደረጋሉ፡-
– ከልደታ ፍርድ ቤት ወደ መስቀል አደባባይ ሜክሲኮ አደባባይ ላይ
– ከአትላስ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ፒኮክ መብራት ላይ
– ከቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ ጠማማ ፎቅ ላይ
– ከቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ባምቢስ መቅረዝ ሆስፒታል መስቀለኛ ላይ )
-ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)
– ከብሔራዊ ቤተመንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ (ብሔራዊ ቤተመንግሥት ላይ)
– ከሜትሮሎጂ ወደ ብሔራዊ ቲያትር ጎማ ቁጠባ መብራት ላይ
– ከተክለ ኃይማኖት አደባባይ በኢምግሬሽን ጥቁር አንበሳ ላይ
– ከንግድ ማተሚያ ወደ ፍልውሃ ንግድ ማተሚያ መስቀለኛ ላይ
– ከቸርችል ወደ ጥቁር አንበሳ መብራት ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ
– ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ ፓርላማ መብራት
– ከሀራምቤ መብራት ወደ ሳንጆሴፍ መብራት ሀራምቤ መብራት ላይ
– ከብሔራዊ ቲያትር ወደ ለገሀር መብራት
– ከሰንጋ ተራ 40/60 ወደ ለገሃር ሠንጋ ተራ 40/60 መታጠፊያ ላይ
– ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሠንጋ ተራ መብራት ሜክሲኮ አደባባይ ላይ
– ከአረቄ ፋብሪካ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ አረቄ ፋብሪካ መስቀለኛ ላይ
– ከልደታ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ባልቻ ሆስፒታል መታጠፊያ ላይ
– ከቫቲካን ኤምባሲ ወደ ሳር ቤት አደባባይ ሳር ቤት አደባባይ ላይ
– ከቅዱስ ዮሴፍ ወደ መስቀል አደባባይ አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ላይ
– ከቅዱስ ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ ወደ ለገሃር ቅዱስ ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ መብራት ላይ መንገዶቹ የሚዘጉ ሲሆን በተጠቀሱት መስመሮች ላይ
ከዛሬ መስከረም 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽት 12፡00 ሠዓት ጀምሮ ተሽከርካሪን አቁሞ መሄድ ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል፡፡