Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ የፍፃሜ ውድድር በመጪው ቅዳሜ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከሁለት ወራት በላይ በብርቱ ፉክክር ሲካሄድ የቆየው የፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ የፍፃሜ ውድድር በመጪው ቅዳሜ መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

በውድድሩ ለፍጻሜ የበቁት ጴጥሮስ ማስረሻ፣ እየሩሳሌም አሰፋ፣ እዮቤል ፀጋዬ እና ኤፍሬም ጌታቸው ብርቱ ፉክክር ይጠብቃቸዋል።

የዕለት አቀራረብ ላይ መሰረት በማድረግ በዳኞች እና በተመልካቾች ድምፅ የውድድሩ አሸናፊ የሚለይ ሲሆን፤ በውድድሩ አንድ እንግዳ በክብር ዳኛነት ይገኛል።

በ13ኛው ሳምንት አራት ምርጥ ተወዳዳሪዎችን ይዞ የፍፃሜ ውድድሩን የሚያካሂደው ፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት የተዘጋጀለት ሲሆን፤ የዋንጫ እና የአዲስ ሙዚቃ ሽልማት ያበረክታል።

ይህን ደማቅ ውድድር በቀጥታ ስርጭት በመጪው ቅዳሜ ከ6:00 ጀምሮ በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሁሉም የሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version