Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ በሴቶች የ3ሺህ ሜትር መሰናክል የነሐስ ሜዳልያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሴቶች የ3ሺህ ሜትር መሰናክል በሲምቦ አለማየሁ አማካኝነት ተጨማሪ የነሐስ ሜዳልያ አግኝታለች፡፡

በርቀቱ ከአትሌት ሲምቦ አለማየሁ በተጨማሪ ኢትዮጵያን የወከለችው ሎሚ ሙለታ 8ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሯን አጠናቅቃለች፡፡

ውድድሩን ኬንያዊቷ አትሌት ፌይዝ ቼሮቲች በበላይነት ያጠናቀቀች ሲሆን፥ ኬንያ በሻምፒዮናው ያገኘችው አራተኛው የወርቅ ሜዳልያ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ባህሬናዊቷ አትሌት ዊንፍሬድ ያቪ በሁለተኛነት በማጠናቀቅ ለሀገሯ የብር ሜዳልያ አስገኝታለች፡፡

በጃፓን ቶኪዮ እየተካሄደ በሚገኘው ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያ እስካሁን ሁለት የብር እና ሁለት የነሐስ ሜዳልያዎችን አግኝታለች፡፡

Exit mobile version