Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሕዳሴ ግድብ መመረቁን አስመልክቶ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የደስታ መግለጫ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቁን አስመልክቶ የደስታ መግለጫ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው።

‘በኅብረት ችለናል’ በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ በሚገኘው የደስታ መግለጫ ሰልፍ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

በዚህም ተሳታፊዎች የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያንን የዘመናት ቁጭት የመለሰ ነው፣ ሕዳሴ ግድብ የአንድነትና የጽናት ውጤት ማሳያ፣ የሕዳሴ ግድብ የአሸናፊነት አክሊል ፣ የማንሰራራት ጅማሮ ምልክት የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን እያሰመ ነው ።

በተጨማሪም መንግስት የጀመራቸውን የልማት ሥራዎች የሚያበረታቱ እና ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ መልዕክቶች እየተላለፉ ይገኛል።

Exit mobile version