አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጤና ዘርፍ አገልግሎቶችን ዲጂታል ለማድረግ እየተሰራ ነው አሉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ስማርት ዲጂታል የጤና አቅርቦት ሰንሰለት ሶሉሽን ለመተግበር የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።
በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት ዶ/ር መቅደስ ዳባ እንዳሉት÷ ስምምነቱ ሕብረተሰቡ ከመድኃኒት አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚገጥመውን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል ነው፡፡
ስምምነቱ ለሕብረተሰቡ በታማኝነት እና ቅልጥፍና አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችል አንስተው÷ የጤና ዘርፉን አገልግሎቶች ዲጂታል ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
የመድኃኒት አቅርቦትን ብቻ ሳይሆን የጤና ተቋማት የሚሰጡት አገልግሎት ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን በቀጣይነት እንደሚሰራም አብራርተዋል።
የኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ በበኩላቸው÷ ስምምነቱ መድኃኒት በመላው ሀገሪቱ በሚጓጓዝበት ወቅት ከእጅ ንክኪ ነጻ በሆነ መንገድ እንዲጓጓዝ የሚያደርግ መሆኑን አስረድተዋል።
አዲስ የሚተገበረው ሥርዓት የኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አሰራርን እንደሚያቀላጥፍ የገለጹት ደግሞ የኢትዮ ቴሌኮም የኢንተርፕራዝ ሶሉሽን ቺፍ ኦፍሰር አቶ ዮሐንስ ጌታሁን ናቸው፡፡
በቅድስት ብርሃኑ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!