Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘንድሮ ኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የኦሮሚያ ክልለ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ጀሚላ ሲንብሩ የኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ህዝብ ባህል መገለጫ መሆኑን ገልጸው÷ ውይይቱ በዓሉ ባህላዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።
ኢሬቻ የሰላም፣ የፍቅርና የወንድማማችነት ተምሳሌት መሆኑን አንስተው÷ በዓሉ በድምቀት እንዲከበር ሁሉም አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በመድረኩ የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ አባገዳዎች፣ ሀደሲንቄዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።
በመርሐ ግብሩ የኢሬቻ በዓሉን በተመለከተ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
የዘንድሮው ኢሬቻ በዓል ኢሬቻ ለሀገር ከፍታ” በሚል መሪ ሐሳብ እንደሚከበርም ተገልጿል።
በፌናን ንጉሤ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Exit mobile version