አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል በግብርና እና ግብርና ነክ ዘርፍ ላይ በተደረገ የሥራ ዕድል ፈጠራ ከ14 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ሥራ ገብተዋል፡፡
በክልሉ የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ታከለ ቤኛ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷በ2018 በጀት ዓመት በግብርና ዘርፍ በቂ የሥራ እድል ለመፍጠር እየተሰራ ነው፡፡
በዚህ መሰረትም በበጀት ዓመቱ ባለፉት ወራት ከ14 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ሥራ እንዲገቡ መደረጉን አስረድተዋል፡፡
በክልሉ 21 ዞኖች በተለያዩ ቦታዎች ወደ ሥራ ለገቡ ዜጎች የመስሪያ ቦታ፣ የእርሻ ትራክተር፣ የማዳበሪያና ሌሎች ግብዓቶችን ማቅረብ ተችሏል ነው ያሉት፡፡
በዘርፉ ያላቸውን ምርታማነት ለማሳደግ የተሟላ ስልጠና እና የገንዘብ ብድር አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
በማኑፋክቸሪንግና በሌሎች ዘርፎች ላይ ለሚሰማሩ ዜጎች የሥራ ዕድል በማመቻቸት ወደ ሥራ እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑንም አብራተዋል፡፡
በታሪክ አዱኛ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!