Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሕዳሴ ግድብ በአብሮነት የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ማድረግ እንደሚቻል አሳይቷል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዳንኤል ዳምጠው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቅቆ መመረቅ በአብሮነት የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ማድረግ እንደሚቻል አሳይቷል አሉ።

የግድቡን መመረቅ አስመልክቶ ‘በኅብረት ችለናል’ በሚል መሪ ሃሳብ በክልሉ ምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡

አቶ ዳንኤል ዳምጠው በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ የኢትዮጵያውያንን የአብሮነት፣ የፅናት እና የይቻላል መንፈስ ያጎለበተ ነው፡፡

የግድቡ ድል አብሮነትን በማጠናከር በጋራ በመሆን ለላቀ ስኬት በመትጋት የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ማድረግ እንደምንችል ማሳያ ነው ብለዋል።

ሌሎች ታላላቅ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ሀገራችንን በሁሉም መስክ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ማድረግ እንችላለን ነው ያሉት ሃላፊው።

የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ሀገራችንን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማድረስ የተጀመሩ ጥረቶች እውን ለማድረግ ጉልበት ይሆናል ሲሉም ገልጸዋል።

መላው ሕዝብ በግድቡ ግንባታ ያሳየውን ተነሳሽነትና ቅንጅታዊ ጉዞ በማጎልበት የበለፀገች ሀገር ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ማጠናከር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን በበኩላቸው ÷ የግድቡ መጠናቀቅ በቀደምት አባቶች ለሀገርና ለሕዝብ ነጻነት የተከፈለበትን የዓድዋን ድል ዳግም ማብሰር መሆኑን ነው ያወሱት፡፡

የውስጥ እና የውጭ ፈተናዎችን በመቋቋም ግድቡን ለፍጻሜ ማብቃታችን ማንኛውንም ፕሮጀክት ማጠናቀቅ እንደምንችል ያሳያል ብለዋል።

የግድቡ መጠናቀቅ የጋራ ትርክትን በማጠናከር ሌሎች ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በራስ አቅም ለመስራት የተጀመረውን ጥረት እንደሚያጠናክር ገልጸዋል፡፡

የዞኑ ማሕበረሰብ ለሕዳሴ ግድብ እውን መሆን ላበረከተው አስተዋጽኦም ምስጋና አቅርበዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version