Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አለም ዓቀፉ የህፃናት አድን ድርጀት ለባህርዳር ከተማ የ42 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አለም ዓቀፍ የህፃናት አድን ድርጅት ለባህርዳር ከተማ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚውል 42 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

በተደረገው ድጋፍ ዙሪያ የክልሉ የኮሮና ቫይረስ መከላከል እና መቆጣጠር ግብረ ሀይል አስተባባሪ ዶክተር ሙሉነሽ አበበ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ እና የባህርዳር ከተማ ክፍለ ከተሞች ኃላፊዎች በተገኙበት ወይይት ተደርጓል።

የምዕራብ አማራ የህጻናት አድን ድርጀት ስራ አስኪያጅ ሙሉቀን እማኙ ድርጀቱ በሀገሪቱ ስድስት ከተሞች ማለትም አዲስ አበባ፣ ባህርዳር፣ ሀዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ አዳማ እና ጅግጀጋ ለተጎጂዎች በምግብ፣ ውሃ እና ጤና ዘርፎች እርዳታ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለትም በባህርዳር ከተማ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ለችግር የበለጠ ተጋላጭ ለሆኑ የህበረተሰብ ከፍሎች የ42 ሚሊየን ብር ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።

ከ42 ሚሊየን ብር ድጋፍ ውስጥ 36 ሚሊየን በቀጥታ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሰጥ እና ቀሪው ለጤና እና ለውሃ አገልግሎት እንደሚውል ነው የተናገሩት።

በድጋፋ 5 ሺህ 536 አባወራዎች እና እማወራዎች እንዲሁም 22 ሺህ 144 የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ነው ስራ አስኪያጁ የገለፁት።

የክልሉ የኮሮና ቫይረስ መከላከል እና መቆጣጠር ግብረ ሀይል አስተባባሪ ዶክተር ሙሉነሽ አበበ በበኩላቸው፥ አለም ዓቀፉ የህፃናት አድን ድርጅት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በቀጣይም በትክክል መረዳት የሚገባቸውን ሰዎች መመልመቻቸውን የሚያረጋግጥ ግብረ ሀይል ከሰራተኛ ና ማህበራዊ ጉዳይ፣ ከጤና፣ ከገንዘብ እና ኢኮኖሚ እና ከውሃ ተቋማት መቋቋም አለበት ብለዋል።

በናትናኤል ጥጋቡ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version